አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአምስት የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ሹመት ሰጡ።
በዚህ መሰረት፦
- አቶ መስፍን መላኩ – በሚኒስትር ዲኤታ ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽህፈት ቤት ሃላፊ
- ዶክተር ሹመቴ ግዛው – የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር
- አቶ ከፍያለው ተፈራ – የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር
- አቶ ወርቁ ጋቻና – የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምር እና ልማት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም
- አቶ ዘላለም መንግስቴ – የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ተሾመዋል።
ሹመቱ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።