የሀገር ውስጥ ዜና

የትምህርት ሚኒስቴር ከሮተሪ ኢንተርናሽናል ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ

By Feven Bishaw

October 01, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር ከሮተሪ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጋር በትምህርቱ ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

የመግባቢያ ሰነዱ በንጹህ ውሃ አቅርቦትና በሌሎችም ትምህርት ነክ ጉዳዮች በጋራ ለመስራት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡