አዲስ አበባ፣ መሰከረም 23፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢፌዲሪ ባህር ሃይል ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም ተቋሙ የሚፈልገውን የሰለጠነ የባህር ኃይል ባለሙያ በማፍራት ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የባህር ኃይል መሠረታዊ ባህርተኞች ማሰልጠኛ ማዕከል ም/አዛዥ ኮማንደር ከበደ ሚካኤል እንዳሉት÷ ቢሾፍቱ እንጂነሪግ የሚገኙትን የባህር ኃይል አባላት በውሃ ዋና የሚሠጡ ግዳጆችን ለመወጣት የሚያስችል ስልጠና ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት ፣ የሃገርን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችልና ከውጭና ከውስጥ የሚመጡ ችግሮችን የሚጠብቅ ዘመናዊ የሆነ ባህር ሃይል ሠራዊት ማደራጀትና ማሰልጠን አስፈላጊ ነው ፡፡