አዲስ አበባ፣ መሰከረም 23፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በኢፌዴሪ ሕገ መንግስት መሠረት ነገ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም በፌዴራል ደረጃ አዲስ መንግሥት ይመሰረታል።
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2፥ በሕዝብ ተመርጦ አዲስ የሚቋቋም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ጊዜውን መጀመር ያለበት በ“መስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ ነው” ብሎ በደነገገው መሠረት ነው ነገ በፌዴራል ደረጃ አዲስ መንግሥት የሚመሠረተው።