የሀገር ውስጥ ዜና

ድንቅ ዝግጅት በማሳካት የተሳተፉትን ሁሉ አመሰግናለሁ – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

By Feven Bishaw

October 05, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትናንት ለተካሄደው በዓለ ሲመት ዝግጅት መሳካት ተሳትፎ ላደረጉ ምስጋና አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ በእንግድነት በመሳተፍ ልዩ ክብራቸውን ላሳዩን ፣ በመልዕክቶቻቸው ልዩ ምኞታቸውን ለገለፁልን አለምአቀፍ ወዳጆቻችን እና አፍሪካዊ ወንድሞቻችን ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል።