የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በቀጠናዊ ዲፕሎማሲና ባለ ብዙ ወገን ትብብር ላይ የተጀመሩ ስራዎችን ልታጎለብት እንደሚገባ ተገለፀ

By Feven Bishaw

October 05, 2021

አዲስ አበባ፣መስከረም፣25፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በቀጠናዊ ዲፕሎማሲ እና ባለ ብዙ ወገን ትብብር ላይ የተጀመሩ ስራዎችን ልታጎለብት እንደሚገባ ምሁራን ተናገሩ ፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ሱራፌል ጌታሁን ÷ኢትዮጵያ በቀጠናዉ ያላትን የጋራ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በዲፕሎማሲዉ መስክ አዳዲስ አሰራሮችን ገቢራዊ ማድረግ እንደሚገባት ተናግረዋል ፡፡