አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በቅንነት መንፈስ በጋራ እንድንሰራ ምክር ቤቱ እንዲቆጣጠረን እና እንዲያግዘን እንፈልጋለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ምክር ቤቱን ጠየቁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የሚቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ ነው ምክር ቤቱ እንዲቆጣጠርን እና እንዲያግዘን እንፈልጋለን ያሉት፡፡
በመንግስት ኃላፊነት ውስጥ መግባባት የማይደረስባቸዉ ጉዳዮች ብዙ ናቸዉ ነገር ግን በሂደት እየተማርን እያሻሻልን ካልሄድን በስተቀር ሁሉን በአንዴ መመለስ አይቻልም ብለዋል፡፡
እንደመንግስት አደረጃጀት ያለብን ችግር የስርዓት ስብራት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሙያዊ የሆነ አደረጃጀትበማስፈለጉ ይህን ችግር በማመን እሱን ማስተካከል አለብን ብለን ነዉ የተነሳነው፤ ብለዋል፡፡
በክልሎች የፌዴራል መንግስቱን ጣልቃ ገብነትን በተመለከተ ለተነሳው ጉዳይ በሰጡት ማብራሪያ፥ ህገ መንግስቱን መሰረት ባደረገ እና ባማከበረ መልኩ የሚከናወን መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የጸጥታ ችግር ስጋትን ለመመከት በዛላቂነት መስራት ያስፈልጋል የተባለውም ተገቢ ሀሳብ ነው ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!