አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የህወሃት የጦር ጀነራሎች ቀረጥ ሳይከፈልበት የገባ ጐማና መሰል የኮንትሮባንድ እቃዎችን በይፋ በወታደራዊ መኪኖች ጭነው ይሸጡ እንደነበር የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገለፁ፡፡
አሸባሪው ህወሓት በመሪነት ጊዜው የንግድ ባንክ፣ የልማት ባንክ እና ሌሎችንም የፋይናንስ ተቋማት እየመዘበረ ኢኮኖሚያዊ አሻጥር በመፍጠር የገንዘብ ምንጭ አድርጓቸው ቆይቷል ነው የተባለው፡፡