የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች አልጋወራሽ ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

October 07, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች አልጋወራሽ ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ነኸያን ጋር በስልክ ተወያይተዋል።

በውይይታቸው በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የወዳጅነትና የትብብር ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረዋል፡፡