የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ የገጠሟትን ፈተናዎች ለመሻገር የአዲሱ ካቢኔ አባላት በከፍተኛ የሀገር ፍቅር ስሜት መስራት አለባቸው – ምሁራን

By Feven Bishaw

October 08, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከውስጥም ሆነ ከውጭ የገጠሟትን ፈተናዎች ለመሻገር የአዲሱ ካቢኔ አባላት በከፍተኛ የሀገር ፍቅር ስሜት መስራት አለባቸው ሲሉ ምሁራን ተናገሩ፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ የነበራቸው የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ የመንግስትና የህዘብ አስተዳደር ተመራማሪ ዶክተር መሀመድ አሊ ÷ ሀገርን የማገልገል መመሪያን የተቀበሉት ሚኒስትሮቹ ኢትዮጵያ ያለችበት ፈታኝ ወቅታዊ ሁኔታን ያገናዘበ ስራን መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል ።