የሀገር ውስጥ ዜና

የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ የስራ ርክክብ አደረጉ

By Feven Bishaw

October 08, 2021

አዲስ አባባ፣ መስከረም 28፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በአዲሱ የመንግስት ምስረታ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ አደም ፋራህ ከቀድሞው የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል፡፡

አቶ ብናልፍ አንዷለምን ጨምሮ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ከፍተኛ አመራሮች በዛሬው እለት ከብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡