የሀገር ውስጥ ዜና

የመከላከያ ስፖርት ክለብ  ለጦር ጉዳተኞች ድጋፍ አደረገ

By Feven Bishaw

October 08, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ስፖርት ክለብ በጦር ሀይሎች ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሚገኙ እና በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸዉ ዜጎች ከ190 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለዉ የአልባሳትና የንጽህና መስጫ እቃዎች ድጋፍ አደረጉ፡፡

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ ብርጋዴር ጄነራል አስፋው ÷ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የሆናችሁና ሀገራችንን ለመታደግ የአካልና የህይወት መስዋዕትነት የከፈላችሁ ጀግኖች በመሆናችሁ መቼም የማይረሳ ታሪክ ሰርታችኋል ብለዋል።