የሀገር ውስጥ ዜና

የጎንደር ከተማና አካባቢውን ሰላም ሊያውክ በሚችል እንቅስቃሴ የሚሳተፉ አካላት ላይ ክትትል እየተደረገ ነው

By Feven Bishaw

October 10, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ከተማና አካባቢውን ሰላም ሊያውክ በሚችል እንቅስቃሴ የሚሳተፉ አካላት ላይ ክትትል እየተደረገ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የህዝቡን ሰላም ሊያውክ የሚችል እንቅስቃሴ ውስጥ የሚሳተፉ አካላት ላይ ጥብቅ ክትትል እየተደረገ መሆኑን የከተማው ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር አየልኝ ታክሎ አስታውቀዋል።