የሀገር ውስጥ ዜና

ለድምጻዊ አህመድ ሁሴን (ማንጁስ) በትውልድ ከተማው ኮምቦልቻ አቀባበል ተደረገለት

By Meseret Awoke

October 10, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የፋና ላምሮት የባለተሰጥኦ ድምፃውያን ውድድር አሸናፊው አህመድ ሁሴን (ማንጁስ) በትውልድ ከተማው ኮምቦልቻ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ባዘጋጀው የድምፃውያን ውድድር የ1ሚሊየን ብር እና የዋንጫ ተሸላሚ የነበረው አህመድ ሁሴን ÷ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የከተማ አስተዳደሩ እና የዞን አመራሮች በተገኙበት በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

የደቡብ ወሎ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኀላፊ አቶ ሱለይማን እሸቱ በአቀባበል ስነስርዓቱ እንዳሉት÷ ድምፃዊ አህመድ ከአሸናፊነት በላይ ወሎ የቅኝት መሠረት መሆኗን አስመስክረሀል ብለዋል፡፡

ለድምጻዊው የተለያዩ ድርጅቶች እና ግለሰቦች 4መቶ ሺህ ብር ማበርከታቸውም ተናግሯል፡፡

በእሸቱ ወ/ሚካኤል

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!