የሀገር ውስጥ ዜና

ሀገር አቀፍ የወባ ሳምንት እየተካሄደ ነው

By Meseret Awoke

October 11, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ወባን ማጥፋት ከእኔ ይጀምራል በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 1 እስከ 7 በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረዉን የወባ ሳምንት ይፋዊ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመርሀ ግብሩ ከጤና ሚኒሰቴር ፣ የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊዎች ፣ የዞንና የወረዳ ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልናመቆጣጠር ዳይሬክተር ወይዘሮ ሕይወት ሰለሞን በሽታውን ለመከለካል የሁሉም ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዘርፉ የሚታየውን ችግር ለመቅረፍም ከባለድርሻ አካለት ጋር ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ብለዋል፡፡

በማቱሳላ ማቴዎስ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!