የሀገር ውስጥ ዜና

ቤተክርስቲያኗ ለተፈናቀሉ ወገኖች2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገች

By Feven Bishaw

October 12, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በሰሜኑ ጦርነት ለተፈናቀሉ እና በደሴ ከተማ መጠለያ ለሚገኙ ወገኖች 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገች፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ መመሪያ ሰጭነት በሽብርተኛው ትህነግ ወረራ ተፈናቅለው በደሴ ከተማ መጠለያ ለሚገኙ ወገኖች በሀገረ ስብከቱ ከገዳማት እና አድባራት እንዲሁም በኢትዮ-በርኖስ ሆቴል አማካኝነት ከማኅበረሰቡ የተሰባሰበ 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ ተደርጓል፡፡