አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ሀረሪ ክልልን ጨምሮ መስከረም 20 ምርጫ በተካሄደባቸው አካባቢዎች በማሰመልከት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ውጤት ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የእንኳን ደስ አለን መልዕክት አስተላልፈዋል።
ርዕሰ መስተዳደሩ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አለን መልዕክት እንዳሉት የሀገራችን ሕዝብ ዝናብና ፀሐይ ሳይበግረው፣ በረጃጅም ሰልፎች ሳይሰላች የሚፈልገውን ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ካለምንም ተፅዕኖ መርጧል።