የሀገር ውስጥ ዜና

የወረዳው አስተዳደር ከሰሜን ወሎ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ

By Meseret Awoke

October 15, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ ከተማ የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 አስተዳደር ከሰሜን ወሎ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ።

ከወረዳው ነዋሪዎች እና ባለሀብቶች ያሰባሰቡትን ከ3 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት አልባሳት እና ምግቦችን ይዘው መምጣታቸው የተናገሩት የወረዳው ንግድ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ደሳለኝ እውነቱ በስፍራው መገኘታችን በተጨባጭ ያለውን ችግር እንድንረዳ አስችሎናል ብለዋል።

ወገን ወገኑን ለመርዳት መንቀሳቀስ አለበት የሚለው ከገርጂ ታክሲ ተራ የመጣው ወጣት ኤርሚያስ÷ ድጋፉን በአንድ ወር ውስጥ ማሰባሰባቸውን መናገሩን ኤኤምኤን ዘግቧል።

ይህንን አሳዛኝ ክስተት በመተባበር እና በመተጋገዝ ልናልፈው ይገባል ያሉት መርጌታ አምደብርሀን ኪዳኔ በበኩላቸው÷ የየትኛውም ሀይማኖት አስተምህሮም ይህንኑ ነው የሚደግፈው ብለዋል።

ለተደረገላቸው ድጋፍ በስልክ አምባ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ያመሰገኑት የደቡብ ወሎ ዞን ሴቶች እና ህፃናት መምሪያ ተወካዩ አቶ አብዬ ተሾመ÷ አሁን ላይ ሁሉም መጠለያ ካምፖች መሙላታቸውን በመግለፅ ድጋፎቹ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!