የሀገር ውስጥ ዜና

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የመዉሊድ በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By Feven Bishaw

October 17, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የመዉሊድ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ከንቲባዋ በመልዕክታቸው በአሉን ስናከብር እንደከዚህ ቀደሙ የተቸገሩትን በመርዳት ፤ ያለንን ለሌሎች በማካፈል፤ የታረዙትን በማልበስ ፤ የወደቁትን በማንሳት ፤ የታመሙትን በመዘየር ፤ ለምድራችን ሰላም ዱአ በማድረግ እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል ።