የሀገር ውስጥ ዜና

ወጣቶችና ሴቶች ሀገር ማዳን ዘመቻውን ለማሳካት የተጠናከረ ተሳትፎ እያደረጉ ነው- ማህበራት

By Feven Bishaw

October 21, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገር ማዳን ዘመቻውን ለማሳካት አባሎቻቸው የተጠናከረ ተሳትፎ እያደረጉ መሆናቸውን የአማራ ክልል ወጣቶችና ሴቶች ማህበራት አስታወቁ።

የማህበራቱ ሊቀ መንበሮች እንደተናገሩት ÷የማህበራቱ አባላት አሸባሪው ህወሃት የከፈተውን ጦርነት ለመመከት ተሳትፎአቸውን እያጠናከሩ ነው። የማህበሩ ሊቀ መንበር ወጣት አባይነህ ጌጡ አባላቱ አሸባሪው ቡድን ከፀጥታ መዋቅሩ ጎን በመሰለፍ የህይወት መስዋትነት በመክፈል ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።