አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በኮምቦልቻ ከተማ ባደረገው ቅኝት በከተማ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መኖሩን ተመልክቷል።
በከተማዋ የሚገኙ የህክምና ተቋማት ፣ መድሀኒት ቤቶች ፣ የንግድ ቤቶች ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሁም የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በመደበኛ ሁኔታ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ማየት ተችሏል።
ቅኝት ባደረግንባቸው የከተማዋ አካባቢዎች ያገኘናቸው ነዋሪዎች እንዳሉትም ÷ ማህበረሰቡ ከሀሰት ኘሮፖጋንዳ ራሱን በማራቅ ሀገሩን ሊጠብቅ ይገባል።
ስራችንን እየሠራን የጁንታውን ሴራ እናከሽፋለን ያሉት ነዎሪዎቹ ÷ ለጸጥታ ሀይሉ ደጀን ከመሆን ጀምሮ ግንባር ድረስ በመሄድ መስዕዋትነትን እየከፈልን ነው ብለዋል።
በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!