አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለ66ኛ ጊዜ ከ4 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ነገ እንደሚያስመርቅ ተገለጸ፡፡
ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሶስተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 4 ሺህ 47 ተማሪዎችን እንደሚያስመርቅ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አለምሸት ተሾመ በተለይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡