የሀገር ውስጥ ዜና

ግጭቶች ባሉባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ሲያስተምሩ የነበሩ መምህራን እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀረበ

By Feven Bishaw

October 31, 2021

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 21፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በመቐለ ፣ በአዲግራት፣በአክሱም ፣በራያና በወልድያ ዩኒቨርስቲዎች ሲያስተምሩ የነበሩ መምህራንን ወደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች በጊዜያዊ ለመመደብ እንዲያስችል እንዲመዘገቡ የትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ፡፡

በዚህም በዩኒቨርሲቲዎቹ ሲስተምሩ የነበሩ መምህራን በሙሉ ከነገ ጥቅምት 22 እስከ 24 ቀን 2014 ዓ.ም በሚኒስቴሩ የፌስቡክ ገፅ ላይ የሚገኘውን ማስፈንጠሪያ (ሊንክ) በመጠቀም እንዲመዘገቡ መጠየቁን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡