የሀገር ውስጥ ዜና

የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት የሚያስገነባው የአይነስውራን ት/ቤት ተጎበኘ

By Feven Bishaw

November 01, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ፅህፈት ቤታቸው እያስገነባ ያለውን የአይነስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ጎብኝተዋል፡፡

ጽህፈት ቤቱ በ400 ሚሊየን ብር የሚያስገነባው ትምህርት ቤት 320 አይነስውራንን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን÷ ለአይነስውራኑ በሚሆን መልኩ እየተገነባ ነው ተብሏል፡፡