የሀገር ውስጥ ዜና

 እንደ በግ የታረደዉን የሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊታችንን አንረሳውም !- ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

By Feven Bishaw

November 02, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘ወገኔ’ ብሎ ባገለገለው አካል እንደ በግ የታረደዉን፤ በክፉዎች ፅዋ ግብዣ መርዝ የተጋተዉን የሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊታችንን መቼም አንረሳውም ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡

ለ 2 አስርት አመታት ‘ወገኔ’ ብሎ በቀበሮ ጉድጓድ ዉስጥ ህይወቱን፣ ቤተሰቡን፣ ኑሮዉን አሳልፎ በሰጠለት አካል በተኛበት የታረደዉን፤ የተካደዉን፤ ከጀርባው የተወጋውን ፤ ዕርቃኑን እንዲዋረድ የተደረገውን፤ በሬሳዉ ዙሪያ ከበሮ የተደለቀበትን ያንን ጀግና የሰሜን ዕዝ ወታደር መቼም አንረሳውም ብለዋል ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፅ ባሰፈሩት ፅሁፍ፡፡