የሀገር ውስጥ ዜና

የሰሜን እዝ በሽብርተኛው ህወሃት ከጀርባው የተወጋበት አንደኛ አመት ነገ ታስቦ ይውላል

By Feven Bishaw

November 02, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን እዝ በሽብርተኛው ህወሃት ከጀርባው የተወጋበት አንደኛ አመት ነገ ጥቅምት 24 ቀን ታስቦ ይውላል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት ምሁራን÷ ድርጊቱ የጭካኔ ጥግ ማሳያ የታሪካችን ጥቁር ገፅ መሆኑን አብራርተዋል።