አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪውን ቡድን ቀብር በማፋጠን ወደ ልማት መዞር አለብን ሲሉ የምዕራብ አየር ምድብ አዛዥ ገለጹ ።
በአየር ኃይል የምዕራብ አየር ምድብ የሰራዊት አባላትና ሲቪል ሰራተኞች አሸባሪው ሕወሓት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት በሰሜን ዕዝ አመራርና የሠራዊት አባላት ላይ የፈፀመው አረመኔያዊ ጥቃት አንደኛ አመት በተለያየ ዝግጅት አስበው ውለዋል ፡፡