የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ ተረጋግታ ወደ ቀደመው የኢኮኖሚ እድገቷ ትመለሳለች – በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር

By Feven Bishaw

November 05, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያውያን የጋራ ጥረት ሃገሪቱ ወደ ቀደመው የኢኮኖሚ እድገቷና መረጋጋቷ ትመለሳለች ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ሁ ፔንግ ገለፁ፡፡

ዳይሬክተሩ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ እንደ ጥሩ ወዳጅ እና አጋር ሃገር ኢትዮጵያ በህዝቧ ጥረት ወደ ቀደመው የኢኮኖሚ እድገቷ እንዲሁም መረጋጋቷ ትመለሳለች ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል፡፡