የሀገር ውስጥ ዜና

በአሸባሪው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሳንበገር ተፈትነን አገራችንን እናሻግራለን – የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች

By Feven Bishaw

November 09, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪው ህወሓት የጥፋት ድርጊትና የሚነዛው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሳይበግራቸው ተፈትነው አገርን ለማሻገር የድርሻቸውን እንደሚወጡ በድሬዳዋ ኢዜአ ያነጋገራቸው የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ገለጹ።

በድሬዳዋ አስተዳደር ከ2 ሺህ 400 በላይ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ፈተናቸውንተረጋግተው እየወሰዱ እንደሚገኙ ተመላክቷል።