አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሬውተርስ በኢትዮጵያ የጸደቀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስመልክቶ ያወጣው ዘገባ ፍጹም ስሕተት መሆኑን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አስታወቀ።
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዜጎች ከመታወቂያ ባሻገር እንደ መንጃ ፈቃድ፣ የሥራ ቦታ መታወቂያ እና ፓስፖርትን አልያም ሌላ ማንነትን የሚገልጽ ማንኛውንም ሕጋዊ ሰነድ እንዲጠቀሙ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በግልጽ ያስቀምጣል፡፡