የሀገር ውስጥ ዜና

የሼህ ሰኢድ ሁሴን የቀብር ስነ ስርዓት ተፈጸመ

By Feven Bishaw

November 12, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ሱመያ መስጅድ ለረጅም አመታት ኢማም ሆነው ያገለገሉት እና ታላቅ የሃይማኖት አባት የሆኑት የሼህ ሰኢድ ሁሴን የቀብር ስነ ስርዓት ተፈጸመ።

ሼህ ሰኢድ በሆስፒታል ህክምና ሲከታተሉ ቆይተው፥ በዛሬው እለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡