የሀገር ውስጥ ዜና

ህወሓት አሁንም ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን በመጣስ ታዳጊዎችን ለጦርነት እያሰለፈ ነው

By Feven Bishaw

November 12, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት አሁንም ዓለም አቀፍ የህጻናት ድንጋጌዎችን በመጣስ ታዳጊ ህጻናትን ለጦርነት እያሰለፈ እንደሚገኝ ተገለጸ።

ቡድኑ በአማራ እና አፋር ክልሎች በፈጸመው ወረራ በተደጋጋሚ ታዳጊ ህጻናትን በጦርነቱ ሲማግድ ቆይቷል፥ አሁንም እየማገደ እንደሚገኝ በወሎ ግንባር የሚገኘው የኤፍ ቢ ሲ ጋዜጠኞች ቡድን አረጋግጧል። ሰሞኑን በወሎ ግንባር ለመከላከያ ሰራዊት እጃቸውን የሰጡ የአሸባሪው ቡድን ምርኮኞች ሁኔታ ይህን ያረጋግጣል።