የሀገር ውስጥ ዜና

ሊቢያ የአዲስ አበባ ኤምባሲዋን እንደዘጋች ተደርጎ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው አለች

By Meseret Awoke

November 17, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሊቢያ አዲስ አበባ የሚገኘውን ኤምባሲዋን እንደዘጋጅ ተደርጎ እየተሰራጨ ያለውን ሀሰተኛ መረጃ አስተባበለች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ኤምባሲው ስራ ላይ መሆኑን እና የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን ለሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

አንዳንድ የአፍሪካ አገራት የአዲስ አበባ ኤምባሲዎቻቸውን መዝጋታቸውን እና ሊዘጉ ዝግጅት እያደረጉ እንደሆነ ተደርጎ የሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ በመንግስት ላይ እየተካሄደ ያለው የውጭ ጫና እና የሥነ ልቦና ጦርነት አካል መሆኑን አምባሳደር ዲና ተናግረዋል፡፡

ሌሎች የተያያዙ መረጃዎች ተጣርተው ለህዝብ ይፋ እንደሚደረጉም ቃል አቀባዩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!