የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያውያን ለክተት ዘመቻው የሰጡት መልስ ጠላትን ተስፋ ያስቆረጠ ነው – የመንግስት ኮሙኒኬሽን

By Meseret Awoke

November 17, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን ለክተት ዘመቻው የሰጡት መልስ ጠላትን ተስፋ ያስቆረጠ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገለግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ከበደ ዴሲሳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፥ ኢትዮጵያውያን ለክተት ዘመቻው የሰጡት ምላሽ የአሸባሪውን ህወሓት ቡድን እኩይ አላማ ህልም ሆኖ እንዲቀር የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡

አገሪቱ የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመረዳት ወጣቱ ከሁሉም የአገሪቷ ክፍሎች የአገር መከላከያ እና የየክልል ልዩ ሀይሎችን በመቀላቀል ላይ መሆናቸውንም ሚኒስትር ዲኤታው አብራርተዋል፡፡

የአገር መከላከያ ሰራዊትን ለማጠናከርም በተያዘው ሳምንት በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች አማካኝነት በርካታ ድጋፎች እየተደረጉ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

በአጠቃላይ ኢትዮጵያውያን በአገር ውስጥ እና በውጭ ለክተት ዘመቻው የሰጡት ምላሽ እና የውጭ ዲፕሎማሲ ጫና እና ጣልቃ ገብነትን ለመመከት ያሳዩት ቁርጠኝነት ጠላትን ተስፋ ያሰቆረጠ ነው ብለዋል፡፡

ህዝቡ ላድረገው ሁለንተናዊ ተሳትፎ ምስጋና ያቀረቡት ሚኒስትር ዲኤታው በቀጣይም ኢትዮጵያውያን ለክተት ዘመቻው መልስ በመስጠት የጠላትን ህልም ማምከን እንድሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!