የሀገር ውስጥ ዜና

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የሚንቀሳቀሱ የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ ተወሰደ

By Feven Bishaw

November 18, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፖሊስ ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይልና ከሚሊሻ አባላት ጋር በመቀናጀት በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የሚንቀሳቀሱ የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ ሰሞኑን የተቀናጀ እርምጃ መውሰዱን የፌደራል ፖሊስ ገለፀ፡፡

በተካሄደው የማጥቃት ዘመቻም በርካታ የኦነግ ሸኔ አባላት መደምሰሳቸውንና አስር ግብረ አበሮቻቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸው እንዲሁም አሸባሪዎቹ በወቅቱ ሲጠቀሙበት የነበረ በርካታ ገንዘብ መያዙ ታውቋል፡፡