አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፖሊስ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ማራቶን ሞተርስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ መጋዘን ውስጥና በመኪኖች ላይ የተከማቸ በርካታ የቤት ክዳን ቆርቆሮ መያዙን አስታወቀ፡፡
ደረጃውንና ጥራቱን ያልጠበቀ የቤት ክዳን ቆርቆሮ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር መግባቱን ተከትሎ ህብረተሰቡ ለፖሊስ ባደረሰው ጥቆማ መሰረት ነው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ኢንተለጀንስ አመራርና አባላት ባደረጉት ክትትል ሊያዝ የቻለው፡፡