አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ የሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ለዘማች ቤተሰቦች የሚሆን ከ250 ሚሊየን ብር በላይ ሀብት እያሰባሰበ መሆኑን አስታወቀ።
የድጋፍ አሰባሰብ እና ተያያዥ ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ዙሪያ ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች የብሎክ አደረጃጀቶችና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ውይይት ተካሂዷል ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምክትል ተጠሪ አቶ አለማየሁ እጅጉ በውይይቱ እንደገለፁት ÷ የህወሓት የሽብር ቡድንና ተላላኪዎች እንዲሁም የውጭ ኃይሎች ኢትዮጵያን ለማፍረስ እያደረጉት ያለው ጥረት በህዝቦች በተባበረ ክንድ እና አንድነት ድል እየተመታ ነው።
የከተማችን ነዋሪዎችም በመንደርና በብሎክ አደረጃጀት በመፍጠር የጀመሩትን የአካባቢ ሰላም እና ጸጥታ ስራ በንቃት በመጠበቅ የጠላቶቻችን ሴራ ለማክሸፍ የጋራ ርብርብ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽነር አቶ አስፋው ተክሌ በበኩላቸው ÷ ‘ከሀሙስ እስከ ሀሙስ’ በሚል በ6ሺህ 885 የብሎክ አደረጃጀት ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና ለዘማች ቤተሰቦች እንዲሁም በጦርነት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚሆን ከ250 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብ ፣የአልባሳት እና የምግብ ቁሳቁስ ሀብት የማሰባሰብ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል ።
ከዚህ በተጨማሪም ከ30ሺህ ዩኒት በላይ ደም ከህብረተሰቡ እንደሚሰበሰብም ኮሚሽነር አስፋው መናገራቸውን ከከተማው ፕረስ ሴክሬታሪ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።
አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!