የሀገር ውስጥ ዜና

አሸባሪው ህወሓት እስኪደመሰስ ለጀግኖቻችን ስንቅ ለማቀበል አንታክትም – የመተማ ሴቶች

By Meseret Awoke

November 18, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በግንባር ለተሰለፉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ያለማቋረጥ ስንቅ በማዘጋጀት ደጀንነታቸውን በተግባር እያሳዩ መሆናቸውን በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ዮሐንስ ከተማ ነዋሪ ሴቶች ተናገሩ።

በዞን ደረጃ በተያዘው ወር ከ20 ሚሊየን ብር ያላነሰ ሃብት ለማሰባሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑም ተመላክቷል።

ኢዜአ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት፥ አሸባሪው የህወሓት ቡድን እስኪደመሰስ ለጀግኖቻችን ስንቅ ለማቀበል አንታክትም ነው ያሉት።

ለህይወታቸው ሳይሳሱ የሀገር ነቀርሳ የሆነውን አሸባሪ ቡድን ለመፋለም በግንባር ለተሰለፉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ያለማቋረጥ ስንቅ በማዘጋጀት ደጀንነታቸውን በተግባር እየሳዩ መሆኑን ተናግረዋል።

“ኢትዮጵያን ለመታደግና ሉዓላዊነቷን ለማስከበር ሁሉም የሚችለውን ማድረግ ይኖርበታል” ሲሉም ገልጸዋል።

ሀገርን ለማዳን ከጠላት ጋር በግንባር እየተፋለመ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊትና ለሌሎች የጸጥታ ሃይሎች ስንቅ ከማዘጋጀት ባለፈ በግንባርም በመሰለፍ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።

በዞኑ የስንቅና ሎጅስቲክ ድጋፍ አስተባባሪ ወይዘሮ ደመቅ አበባው በበኩላቸው፤ ህዝቡ የሚያደርገው ተጋድሎና የደጀንነት ሚና አሸባሪውን ፈጥኖ ለመደምሰስ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።

ለዚህም የተለያዩ የሴት አደረጃጀቶች ድጋፍ በማሰባሰብና ስንቅ በማዘጋጀት ሃላፊነታቸውን እየተወጡ እንደሚገኙም ነው ያስረዱት ።

በዞኑ ባሉ ሦስት የከተማ አስተዳደሮችና አራት ወረዳዎች ቀጣይነት ያለው የስንቅ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አስተባባሪዋ ተናግረዋል።

እንደ እአስተባባሪዋ ገለጻ፤ ለአንድ ሳምንት ብቻ በተደረገ እንቅስቃሴ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ስንቅ ተዘጋጅቶ በግንባር ለሚገኙ የጸጥታ አካላት እንዲደርስ ተደርጓል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!