የሀገር ውስጥ ዜና

የአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ልዩ መልእክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አዲስ አበባ ገቡ

By Meseret Awoke

November 18, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ልዩ መልእክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አዲስ አበባ መግባታቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።

ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በመገናኘት ፣ የሰላም መፍትሔ በማፈላለግ ሂደታቸው የደረሱበትን ሐሳብ እንደሚያብራሩ ነው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የገለጸው።

በተጨማሪም በሰብአዊ ርዳታ ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

ኦባሳንጆ በዚሁ ቆይታቸው መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአፍሪካ ኅብረት አምባሳደሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ እስካሁን በደረሱባቸው ነጥቦች ዙሪያ ማብራሪያ እንደሚሰጡ ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!