አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ2 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።
የኮርፖሬሽኑ አመራርና ሰራተኞች በአሸባሪው ህወሓት ወራሪ ኃይል ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች “ሁልጊዜም ከጎናችሁ ነን!” በሚል ድጋፍ ማድረጋቸውን ለኢዜአ በላከው መግለጫ አመላክቷል።
ኮርፖሬሽኑ ከ2 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው 590 ኩንታል የስንዴ ዱቄትና የተለያዩ አልባሳት ለአደጋ ስጋትና አመራር ምክትል ኮሚሽነር አይደሩስ ሃሰን ማስረከቡን ገልጿል።
በተጨማሪም ኮርፖሬሽኑ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሁለት ዙር 14 ሚሊየን ብር ድጋፍ በማድረግና ደም በመለገስ ለሠራዊቱ አለኝታነቱን ማሳየቱ ተመላክቷል፡፡