የሀገር ውስጥ ዜና

“አሸባሪው ሕወሓት በሥልጣን ዘመኑ ሌብነት እንዲስፋፋ አድርጓል” – የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት

By Feven Bishaw

November 21, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ሕወሓት በሥልጣን ዘመኑ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ላይ ኢ-ፍትሃዊነት እንዲነግስና ሌብነት እንዲስፋፋ በማድረግ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የባንኩ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሐንስ አያሌው ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ÷ይሰጡ የነበሩ ብድሮች በአግባቡ ያልተመሩ እና የተበላሸ የብድር አመላለስ ሂደቶች የሚስተዋልባቸው ብሎም የማይመለሱ ብድሮች ነበሩ ብለዋል፡፡