አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በአንድ ግለሰብ የሸቀጣ ሸቀጥ መደብር ውስጥ ተቀጣጣይ ቁሳቁሶችና ኬሚካሎች መያዛቸው ተገለፀ፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊሰ ኮሚሽን ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ተቀጣጣይ ቁሳቁሶችናኬሚካሎችን ሸቀጣ ሸቀጦችን እንደሽፋን ተጠቅሞ በመደብሩ ውስጥ ደብቆ የተገኘው ግለሰብ በአሁኑ ወቅትነዋሪነቱን በሳውዲ አረቢያ ያደረገ አቶ መሀመድ ሀሰን የተባለ ግለሰብ መሆኑን ጠቅሷል፡፡