የሀገር ውስጥ ዜና

ህብረተሰቡ ሳይዘናጋ የኮቪድ- 19 ክትባትን ሊወስድ ይገባል

By Meseret Awoke

November 21, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ህብረተሰቡ ባልተገባ ወሬ ሳይዘናጋ የኮቪድ 19 ክትባትን በመውሰድ እራሱን ከበሽታው ሊጠብቅ እንደሚገባ የጅማ ዩኒቨርሲቲ አሳሰበ።

በጅማ ከተማ ከነገ ጀምሮ ለ34 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲሁም እንደ ጅማ ዞን በሚቀጥሉት አስር ቀናት ለ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሰዎች የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት እንደሚሰጥ ተመላክቷል።

የጅማ ዩኒቨርሲቲ የአደጋ ጊዜ ትግበራ ማእከል የቫይረሱን ስርጭትና የክትባቱ አሰጣጥ ተግዳሮትን በማስመልከት የውይይት የመድረክ አካሂዷል።

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህርና ሀኪም ፕሮፌሰር ኢሳያስ ከበደ በወቅቱ አንዳሉት ÷ ከኮቪድ 19 ክትባት ጋር ተያይዞ የሚነገሩ ያልተገቡ ወሬዎች ህብረተሰቡን እያዘናጉ ነው።

ከክትባቱ ጋር በተያያዘ የሚናፈሱ ያልተረጋገጡ ወሬዎች ህብረተሰቡ ክትባቱን በጥርጣሬ አንዲመለከተው ያደረገው መሆኑን ጠቁመው ÷ ህብረተሰቡ ባልተገቡ ወሬዎች ሳይዘናጋ ክትባቱን በመውሰድ እራሱን ከበሽታው ጥቃት እንዲጠብቅ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል ።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!