አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪውን የትህነግ ወራሪ ኃይል ለመደምሰስ የወገን ጦር በዋግኽምራ ግንባር በጀግንነት በመፋለም ላይ ይእንደሚገኝና ወራሪው ኃይል ሳይደመስስ እንደማይመለሱ በግንባሩ የክተት ጥሪ ዘማቾች ገልጸዋል።
የወገን ጦር ጠላትን አይቀጡ ቅጣት መቅጣት በሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።
የክተት ጥሪ ዘማች አብዩ ታረቀኝ የክተት ጥሪውን ተቀብለው አሸባሪውን ወራሪ ኃይል ለመፋለም በዋግ ግንባር ተገኝተዋል።
አሸባሪውና ወራሪው ቡድን እስኪደመሰስ በቁርጠኝነት እንደሚፋለሙ ነው የገለጹት።
ወጣቶች ግንባር ድረስ በመዝመት ከጠላት ጋር ከመፋለም ባለፈ በስንቅ ዝግጅትና በሌሎች ሎጀስቲክስ አቅርቦት ትግሉን ማጠናከር ይገባቸዋል ብለዋል።
ሌላኛው አስተያየት ሰጭ አሌ መልካሙ እንዳለው ፥ ወራሪው የትህነግ ኃይል በአማራ ላይ በፈጸመው ግድያ፣ ሀብት ዘረፋና ውድመት ወደ ግንባር እንዲዘምት አስገድዶታል።
መኖር የሚቻለው ሀገር ሲኖር በመሆኑ አሸባሪና ወራሪ ኃይሉን ሳይደመሰስ እንደማይመለስ ነው የተናገረው።
የክተት ጥሪ ዘማች ሻንበል ፈቃዱም እንዲሁ ፥ ኢትዮጵያን ካጋጠማት የህልውና አደጋ ለመታደግ ከወንድማቸው ጋር ወደ ግንባር መዝመታቸውን ተናግረዋል።
ሀብት እና ንብረት ማፍራት፣ ቤተሰብም መምራት የሚቻለው ሀገር ሰላም ሲሆን እንደሆነ ያነሱት ዘማቹ ፥ ወጣቶች በአማራ ላይ እየደረሰ ያለውን ሞት፣ መፈናቀል እና ዘረፋ ለማስቆም ሁለገብ ትግል ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
“በሕልውናችን ላይ የተቃጣውን አደጋ ለመመከት ብቸኛው አማራጭ ክንዳችን ነው” ሲሉም ተናግረዋል።
በአካባቢው ከሚገኘው የወገን ጦር አዛዦች አንዱ እንዳሉት ፥ በዋግኽምራ ግንባር የሚገኘው የወገን ጦር እያደረገ ባለው የጀግንነት ተጋድሎ የጠላትን ኃይል እንቅስቃሴ መግታት ተችሏል።
የወገን ጦር ጠላትን አይቀጡ ቅጣት መቅጣት በሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝም አስረድተዋል።
እየተካሄደ ባለው የህልውና ዘመቻ የደጀኑ ሕዝብ ድጋፍ ለወገን ጦር ትልቅ የሞራል ስንቅ እንደሆነውም ነው የተናገሩት።
የሽብር ኃይሉ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ አንዱ የውጊያ ስልቱ እንደሆነ ያነሱት ኮሎኔሉ ፥ ማኅበረሰቡ ይህንን ተገንዝቦ በጠላት ወሬ መረበሽ እንደሌለበት ማስገንዘባቸውን የአሚኮ ዘገባ ያመለክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!