የሀገር ውስጥ ዜና

መደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ በጤናው ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 167 ተማሪዎች አስመረቀ

By Meseret Awoke

November 21, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሻሸመኔ ካምፓስ በጤናው ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 167 ተማሪዎች ዛሬ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ አስመረቀ።

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሻሸመኔ ካምፓስ ፕሬዝዳንት ዶክተር ቢፍቱ ገዳ በስነ ስርአቱ ላይ እንደተናገሩት፥ ካምፖሱ ዛሬ ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ለ5ኛ ጊዜ ነው።

ዶክተር ቢፍቱ፥ የጤና ሙያ ከሌሎች ሙያዎች በተለየ ሁኔታ ውድ የሆነውን የሰው ህይወት የማትረፍ ስራ ስለሆነ፥ ተማራቂዎች ሰውን ከሰው ሳይለዩና ሥነ ምግባር በረላበሰ መልኩ ሕብረሰስቡን ማገልገል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደክተር አህመድ ከሊል በበኩላቸው፥ “መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ከተቋቋመበት ቀን ጀምሮ በተለያየ ሙያ በርካታ ተማሪዎችን አስመርቆ ለቁምነገር አብቅቷል” ብለዋል።

ዛሬም በጤናው ዘርፍ 121 ተመራቂዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 46 ተመራቂዎችን ደግሞ በሁለተኛ ድግሪ ማስመረቁን ተናግረዋል።

ተመራቂ ተማሪዎች በተማሩበት ሙያ ህዝቡን በታማኝነትና በታታረነት እንድታገለግሉም በአደራ ብለዋል።

በአዋላጅ ነርስ የተመረቀችው ኮኮቤ ቦጋሌ “በተመረኩበት ሙያ ሰው መሆኑን ብቻ መሰረት አድርጌ ላገለግል ተዘጋጅቻለሁ” ብላለች።

በጤና መከንን በከፍተኛ ውጤት የተመረቀው መሐመድ ገመዳ በበኩሉ፥ “በጤና ሙያ መመረቅ የሰውን ህይወት ለማትረፍ በመሆኑ ተግቼ እሰራለሁ” ሲል ቃል ገብቷል።

መደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ በ13 ዙር ከ36 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በተለያዩ ትምህርት መስኮች ማስመረቁ ታውቋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!