አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በፖለቲካዊ ድርድርም ሆነ በወታደራዊ ኃይል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ከስልጣን አንስቶ የሽግግር መንግሥት ለመመስረት የሚደረገውን ሙከራ እንደሚቃወሙ የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ካረን ባስ ገለጹ፡፡
“በፖለቲካዊ ድርድር፣ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም በወታደራዊ ኃይል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ከስልጣን አንስቶ የሽግግር መንግሥት ለመመስረት” የሚሰነዘረውን ዛቻ እንደሚቃወሙ የአሜሪካ ኮንግረስ አባል እና የኮንግረሱ የውጭ ጉዳይ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ካረን ባስ አስታወቁ፡፡
ካረን ባስ በድረ ገጻቸው ዛሬ ባወጡት መግለጫ ይህን በህወሓት እና ሸኔ የሽብር ቡድኖች እና ሌሎች ተቃዋሚ ኃይሎች የሚሰነዘረውን ማስፈራሪያ እንደማይቀበሉት መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
“በኢትዮጵያ አስተዳደራዊና የግዛት አንድነት ላይ የተቃጣው እና የመላ ቀጣናውን ሰላምና ደህንነት የሚገዳደረው ይህ ግጭት በወታደራዊ መፍትሔ የሚፈታ አይደለም” ሲሉ ካረን ባስ በኃይለ ቃል ጭምር አስረግጠው ተናግረዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!