አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) መሰረታዊ ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአካባቢው ወጣቶች ተመርቀዋል።
በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰጠኝ አወቀ ÷ የሀገር ደህንነት ጉዳይ የሁሉም በመሆኑ የተማረው አካልም በህልውና ዘመቻው መሳተፉ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዋል።
እንዲሁም ከወታደራዊ ዝግጅት በተጨማሪ የዘማች ቤተሰቦችን በምንችለው ሁሉ ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅብን አሰልጣኝ ሻንበል ስንታየሁ መዝገቡ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ማሳሰባቸውን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ካሳሁን ተገኘ በበኩላቸው ÷ “ለራሳችን ከራሳችን ውጭ ማንም አይደርስልንምና አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ ለነገ የማይባል ጉዳይ ነው” ብለዋል።
“ጀግንነት የአባቶቻችን ነውና ማንም አያንበረክከንም ” ያሉት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ቢኒያም ጫቅሉ ለአሰልጣኞችና ፕሮግራሙን ለአዘጋጁ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።
“በአማራ ህልውና ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመጋፈጥ ሁላችንም በአካልና በአእምሮ መዘጋጀት ይገባናል”የሰልጣኞች መልእክት ነው።
አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!