የሀገር ውስጥ ዜና

ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት የታወቁት የምዕራባውያን ሚዲያዎች በሱዳን መዶለታቸው ተሰማ

By Meseret Awoke

November 21, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ላይ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት የታወቁት የምዕራባውያን የሚዲያ ተቋማት ተወካዮች በካርቱም በሚደረግላቸው ድጋፍ በሱዳን ዋድ ሙዛሚል ከተማ መሰብሰባቸው ተገለጸ።

በካርቱም መንግስት በሚደረግላቸው ድጋፍ በጋራ ሱዳን ዋድ ሙዛሚል ከተማ ውስጥ እየዶለቱ ያሉት የሲ ኤን ኤን ፣ ቢቢሲ አፍሪካ፤ ሬውተርስ አፍሪካ፥ አሶሽትድ ፕሬስ፥ ቴሌግራፍ፥ የፍራንስ24 እና የአልጀዚራ ወኪሎች መሆናቸው ታውቋል።

የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ዲፕሎማሲ ተንታኝ የሆኑት ኬንያዊው ኮሊንስ ዋንዴሪ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፥ በአሸባሪው ህወሃት የሚፈበረኩ የሀሰት መረጃዎችን ሱዳን ለማሰራጨት መዘጋጀቷንም ገልጸዋል።

የሥነ ልቡና ጦርነት ለማካሄድ ያስችላሉ ያሏቸውን ሀሰተኛ መረጃዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ሊለቁ እንደሚችሉም ጠቁመዋል።

ዋድ ሙዘሚል፥ በሱዳን ገዳሪፍ ክልል ከዋና ከተማዋ ካርቱም በስተምስራቅ 450 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!