የሀገር ውስጥ ዜና

የጉራጌ ዞን ለመከላከያ ሰራዊት ከ101 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

By Meseret Awoke

November 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገር መከላከያ ሰራዊትን ለመደገፍና ደጀን ለመሆን እስካሁን ከ101 ሚሊየን ብር በላይ የተለያዩ ድጋፎች ማድረጉን የጉራጌ ዞን አስተዳደር ገለፀ።

ጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊትን ለመደገፍና ደጀን ለመሆን ብሎም በግንባር ከመከላከያው ጋር በመሆን ለአገር ለመዋደቅ የዞኑ ህዝብና ወጣቶች፣ ከመከላከያ በክብር ተሰናባቾችና ተጠባባቂ ብሄራዊ ሀይሎች እንዲሁም አመራሩ እያደረጉት ያለው ተሳትፎ ታሪክ የማይረሳውና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት አኩሪ ተግባር ነው ተብለዋል።

የዞኑ ከፍተኛ አመራር በዞኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አተገባበርና ሌሎችም አገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በወልቂጤ ከተማ ውይይት እያካሄደ ነው።

ህዝቡን በተገቢው በማደራጀትና ግንዛቤ በመፍጠር የአካባቢን ሰላም መጠበቅና ማስጠበቅ ወቅታዊና አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑንም ገልፀዋል።

የተከፈተብን የኢኮኖሚ ጦርነት ለመመከትና እንደ አገር ሊያጋጥመን የሚችለው የምርት ጉድለት ለመሙላት የደረሱ ምርቶች አሰባሰብና ሌሎችም ወቅታዊ የመስኖ ስራዎችና የገቢ አሰባሰብ በትኩረት መምራት ይገባል መባሉን የጉራጌ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!