የሀገር ውስጥ ዜና

የሀዲያ ዞን የመንግስት ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ከ76 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

By Meseret Awoke

November 22, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የሀዲያ ዞን የመንግስት ሰራተኞች ለአገር መከላከያ ሰራዊት ከ76 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸውን የዞኑ መንግስት ረዳት ተጠሪና የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ሀብት አሰባሳቢ ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደገፈ ታደለ ገለፁ።

የዞኑ ነዋሪዎች ለአገር መከላከያ ሰራዊት ከ166 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የዓይነትና ጥሬ ገንዘብ በአራት ዙር ገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቅሰው፥ ከዚህ ውስጥ 76 ሚሊየን ብሩ ከመንግስት ሰራተኞች በጥሬ ገንዘብ የተሰበሰበ መሆኑን ተናግረዋል።

ሰራተኞቹ አገርን በማፍረስ ሴራ የተጠመደው አሸባሪው ህወሓትና ግብረ አበሩ ኦነግ ሸኔ የከፈቱብንን ጦርነት ለመመከት እየተዋደቀ ላለው ለጀግናው የአገር መከለከያ ሰራዊት ከመላው የዞኑ ነዋሪዎች ጋር በመሆን ለሰራዊቱ አለኝታነታቸውን ለመግለፅ ድጋፉን ማድረጋቸው ተጠቁሟል።

በዞኑ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ለሰራዊቱ ከደመወዛቸው አሁንም ተቆራጭ በማድረግ ድጋፋቸውን አጠናክረው መቀጠላቸውንም ነው የተናገሩት።

እንደ ዞን እየተደረገ ያለው የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተጠናክሮ መቀጠሉን የጠቆሙት አቶ ደገፈ ÷ ለአምስተኛ ዙር ለሚደረገው ድጋፍ ማሰባሰቢያ በእንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውንም አክለው ገልፀዋል።

መላው የሀዲያ ዞን ነዋሪና የመንግስት ሰራተኞች ለጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት እያበረከቱ ላለው የሀብት ማሰባሰብ ድጋፍ ማመስገናቸውን ከደቡብ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!